2016 በጀት ዓመት የኢትዮጵያን ዕድገት ያስቀጠልንበት ዓመት ነው -ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ - ኢዜአ አማርኛ
2016 በጀት ዓመት የኢትዮጵያን ዕድገት ያስቀጠልንበት ዓመት ነው -ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 2/2016(ኢዜአ)፦ 2016 በጀት ዓመት የኢትዮጵያን ዕድገት ያስቀጠልንበት ዓመት ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
ተጠሪነታቸው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሆኑ አስፈጻሚ ተቋማት የ2016 በጀት ዓመት አፈጻጸምና የ2017 ዕቅድ የግምገማ መድረክ እየተካሄደ ነው።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር የተጠናቀቀው በጀት ዓመት በብዙ መልኩ ስኬት የተመዘገበበት ነበር ብለዋል።
በዚህም የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ እድገት ማስቀጠል ተችሏል ነው ያሉት።
ለሰላም የተሰጠው ትኩረትም ለልማት ሥራዎች ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ገልጸው፥ አሁንም ቀሪ ሥራ ይጠይቃል ብለዋል።
መንግሥት በ2017 በጀት ዓመት መግቢያ ወደ ተሟላ ማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራ መግባቱ ትልቅ ዕርምጃ እንደሆነም ገልጸዋል።
ከዚህ አኳያ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጠሪ የሆኑ ተቋማት ለማሻሻያው ትግበራ ስኬት በምሳሌነት የሚወሰዱ ተግባራትን እንዲያከናውኑ አሳስበዋል።
በመድረኩ ተጠሪ ተቋማት የአፈጻጸምና የዕቅድ ሪፖርታቸውን በማቅረብ ላይ ናቸው።