ቀጥታ፡

በጋምቤላ ክልል ኮደርስ ዲጂታል ስልጠና ከ47 ሺህ የሚበልጡ ወጣቶችን ተሳታፊ ይሆናሉ

ጋምቤላ ፤ ነሐሴ 1/2016(ኢዜአ)፦ በጋምቤላ ክልል  በኢትዮጵያዊያን ኮደርስ ዲጂታል ስልጠና ከ47 ሺህ የሚበልጡ ወጣቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ መታቀዱን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተንኩዌይ ጆክ አስታወቁ።

አቶ ተንኩዌይ ጆክ ለኢዜአ እንደገለጹት ለሶስት ዓመት የሚተገበረውን ኢትዮጵያዊያን ዲጂታል የክህሎት ስልጠና ስኬታማ ለማድረግ እየተሰራ ነው።

እንደ ሃገር ለሶስት ዓመት ሊተገበር በታሰበው የኮደርስ ዲጂታል ክህሎት ስልጠና በክልሉ ከ47 ሺህ 280 በላይ ወጣቶችን የስልጠናው ተጠቃሚ ለማድረግ  እየተሰራ ነው ብለዋል።

በክልሉ የታቀደው የኢትዮጵያዊያን ኮደርስ ስልጠናም በሶስት ዙር ተከፍሎ እንደሚሰጥ ጠቁመው፤ በመጀመሪያው ዙር በተያዘው በጀት ዓመት ከ11 ሺህ 820 በላይ ወጣቶችን የስልጠናው ተጠቃሚ ለማድረግ መታቀዱን አስረድተዋል።

በክልሉ ስልጠናውን የሚያስተባብር የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የተካተቱበት ግብረ ሃይል ተቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱን አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያዊያን ኮደርስ ዲጂታል ስልጠና እንደ ሀገር በቀጣዮቹ ሶስት ዓመታት አምስት ሚሊዮን ዜጎችን በማብቃት በሀገሪቷ የታለመውን የዲጂታል ኢኮኖሚን ለማሳለጥ የታለመ የሰው ኃይል ልማት መሆኑ ታውቋል። 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም