ቀጥታ፡

በሴቶች 5 ሺህ ሜትር ሩጫ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ሳይቀናቸው ቀርቷል

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 29/2016(ኢዜአ)፦ በ33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች በ5000 ሜትር ሴቶች የፍጻሜ ውድድር የኢትዮጵያ አትሌቶች ድል አልቀናቸውም።

ኬንያዊቷ አትሌት ቢትሪስ ቺቤት የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች።

በውድድሩ አትሌት እጅጋየሁ ታዬ 14 ደቂቃ ከ32 ሴኮንድ ከ98 ማይክሮ ሴኮንድ አምስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። አትሌት መዲና ኢሳ 14 ደቂቃ ከ35 ሴኮንድ ከ43 ማይክሮ ሴኮንድ ሰባተኛ ወጥታለች።

የርቀቱ የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤት ጉዳፍ ፀጋይ 14 ደቂቃ ከ45 ሴኮንድ ከ21 ማይክሮ ሴኮንድ ስምንተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።

ኬንያዊቷ ቢትሪስ ቺቤት፣ በትውልድ ኢትዮጵያዊ በዜግነት ኔዘርላንዳዊ ሲፋን ሀሰንና ጣልያናዊቷ ናዲያ ባቶክሌቲ ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል።

በ5000 ሜትር ውድድር ኬንያዊቷ አትሌት ፌዝ ኪፕዬጎን ሁለተኛ ወጥታ የነበረ ቢሆንም በውድድሩ 4000 ሜትር ላይ በአትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ላይ በሰራችው ጥፋት ውጤቷ በዓለም አትሌቲክስ ተሰርዟል።

ይህንንም ተከትሎ አትሌት ሲፋን ሀሰን የብር እንዲሁም ጣልያናዊቷ ናዲያ ባቶክሌቲ የነሐስ ሜዳሊያ አግኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም