ኢትዮጵያና ጃፓን የስታርታፖች ስነ-ምህዳር ግንባታ ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያና ጃፓን የስታርታፖች ስነ-ምህዳር ግንባታ ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 27/2016(ኢዜአ)፦ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የጃፓን ዓለም ዓቀፍ የትብብር ኤጀንሲ የስታርታፖች ስነ-ምህዳር ግንባታ ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል የስምምነት ሰነድ ፈርመዋል።
የስምምነቱ ፕሮጀክት በቀጣይ ሦስት ዓመታት የሚተገበር ሲሆን፤ የስታርታፕ ልማት ስርዓት ከአለም አቀፉ ጋር የማስተሳር ስትራቴጂን ማዘጋጀት፣ ስታርታፖችን ማፍራትና በዓለም አቀፍ ሀገራት ቢዝነሳቸውን በማስፋት ከኢንቨስተሮች ጋር በጋራ መስራት እንዲችሉ ያለመ ነው።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ባይሳ በዳዳ (ዶ/ር ) ስታርታፖች አዳዲስ ምርቶችን በማውጣትና ሀብትን በመፍጠር በመፍጠር የኢኮኖሚ ዕድገቱ ላይ ከፍተኛ አስተዋጽዖ የሚያደርጉ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የተደረገው ስምምነት ስታርታፖች ለሚያጋጥሟቸው ፈተናዎች ድጋፍ ለማድረግና ለስነ ምህዳሩ መሳለጥ ጉልህ ሚና እንደሚኖረው አንስተዋል።
የጃፓን ዓለም ዓቀፍ የትብብር ኤጀንሲ ተወካይ ሳቶሜ ጁን በበኩላቸው የጃፓን መንግስት ለፕሮጀክቱ ተግባራዊነት በትኩረት እየሰራ መሆኑን ተነግረዋል።
በዚህም በኬኒያ፣ በታንዛኒያ እና በኢትዮጵያ ለማከናወን የሰው ኃይል እና በጀት በመመደብ በቅርቡ ትግበራውን እንደሚጀምር ገልጸዋል።
የጃፓን መንግስት በ JICA በኩል ለኢትዮጵያ ስታርታፖች ዕድገት እና መስፋፋት በርካታ ድጋፎችን እያደረገ መሆኑን ጠቅሰው የተደረገው ስምምነትም ድጋፉ ይበልጥ አቅም እንደሚፈጥር መጠቆማቸውን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።