የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአሜሪካ የትራንስፖርት ደህንነት አስተዳደር የተቀላጠፈ የኤርፖርት ውስጥ የደህንነት ፍተሻ ፕሮግራም አባል ሆነ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአሜሪካ የትራንስፖርት ደህንነት አስተዳደር የተቀላጠፈ የኤርፖርት ውስጥ የደህንነት ፍተሻ ፕሮግራም አባል ሆነ
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 26/2016(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአሜሪካ የትራንስፖርት ደህንነት አስተዳደር (Transportation Security Administration-TSA) የተቀላጠፈ የኤርፖርት ውስጥ የደህንነት ፍተሻ ፕሮግራም አባል ሆነ።
የዚህ ፕሮግራም አባልነት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሚበርባቸው በአሜሪካ ከሚገኙ ኤርፖርቶች የሚነሱ መንገደኞች የተቀላጠፈ፣ ይበልጥ ምቹ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የቅድመ በረራ አገልግሎት እንዲያገኙ እንደሚያስችላቸው ከአየር መንገዱ ማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።