የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ለተጎጂ ወገኖች 1 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር የሚገመት የምግብና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ለተጎጂ ወገኖች 1 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር የሚገመት የምግብና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች
ሳውላ ጎፋ ፤ሐምሌ 25 / 2016(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች 1 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር የሚገመት የምግብና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች ።
በቤተክርስቲያኗ የሆሳዕናና የሶዶ ሀገረስብከት ሀዋሪያዊ አስተዳደሪ አቡነ ስዩም ፍራንሷ ድጋፉን ለጎፉ ዞን አስተዳደር አስረክበዋል ።
አቡነ ስዩም ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት፤ በወገኖቻችን ላይ የደረሰው አሰቃቂ አደጋ በሰማን ጊዜ እንደ ቤተክርስቲያን እጅግ አሳዝኖናል ብለዋል።
ቤተክርስቲያኗ ቀጣይነት ባለው መልኩ ዘላቂ የመልሶ ማቋቋም ሥራ ላይም ድጋፏን እንደምታጠናክር አረጋግጠዋል ።
ድጋፉን የተረከቡት የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ፤ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ላደረገችው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።