አብያተ ክርስቲያናቱ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ምክንያት ቤተሰቦቻቸውን ላጡና ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረጉ - ኢዜአ አማርኛ
አብያተ ክርስቲያናቱ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ምክንያት ቤተሰቦቻቸውን ላጡና ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረጉ
ሳውላ፤ ሐምሌ 24/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ-ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ደቡብ ምዕራብ ሲኖዶስ እና የደቡብ ምዕራብ ቀጠና ቃለ ሕይወት ቤተ-ክርስቲያን እያንዳንዳቸው የ200 ሺህ ብር ድጋፍ አድርገዋል።
የሃይማኖት ተቋማቱ ድጋፉን ለጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ አስረክበዋል።
ድጋፉን የተረከቡት የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ የሃይማኖት ተቋማቱ ላደረጉት ድጋፍ በዞኑ አስተዳደርና በተጎጂዎች ስም ምስጋና አቅርበዋል።
ተጎጂዎችን ለመደገፍና በዘላቂነት ለማቋቋም የሚረዱ ተግባራት በቅንጅት በመከናወን ላይ እንደሚገኙም ዋና አስተዳዳሪው ገልጸዋል።