ቀጥታ፡

የፌዴራል ፖሊስ የሀገርን ሰላምና ደኅንነትን ከማስጠበቅ ባሻገር ለችግሮች አጋዥና ደጋፊ በመሆን ሕዝባዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ነው - ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 23/2016(ኢዜአ)፦ የፌዴራል ፖሊስ የሀገርን ሰላምና ደኅንነትን ከማስጠበቅ ባሻገር ለችግሮች አጋዥና ደጋፊ በመሆን ሕዝባዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል ገለጹ።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በጎፋ ዞን በመሬት መንሸራተት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ አድርጓል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል፤ ለተጎጂዎች የተላከውን ድጋፍ አስረክበዋል።

በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በአደጋው ምክንያት ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖችም ኮሚሽነር ጄኔራሉ ሐዘናቸውን ገልፀዋል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ አደጋው ከደረሰበት እለት ጀምሮ የፌደራል ፖሊስ አባላት በሥፍራው በመገኘት ሙያዊ እገዛ እያደረጉ መሆኑን ተናግረዋል።


 

በዛሬው እለት ደግሞ በተቋሙ የ4 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ግምት ያላቸው የተለያዩ ቁሳቁሶችና ምግብ-ነክ ድጋፎች መደረጋቸውን ገልፀዋል።

በቀጣይም ሠራዊቱ ከደመወዙ ለመለገስ ዝግጁ መሆኑን ጠቁመው፤ እገዛና ድጋፉ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ተናግረዋል።

የፌደራል ፖሊስ የሀገርን ሰላምና ደኅንነት ከማስጠበቅ ባሻገር ለችግሮች አጋዥና ደጋፊ በመሆን ሕዝባዊ ኃላፊነቱን መወጣቱን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።


 

በፌደራል ፖሊስ የወንጀል መከላከል አስተዳደር እና ድጋፍ ዋና መምሪያ ኃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ነብዩ ኢሳያስ፤ ለአደጋው ተጎጂዎች የቁሳቁስና የምግብ ድጋፍ መደረጉን ገልፀዋል።

ከአደጋው እለት ጀምሮ በሥፍራው በርካታ የሠራዊቱ አባላት በተልዕኮ ላይ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ በዛሬው እለትም ድጋፍ መደረጉን ተናግረዋል።

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም