ፌደራል ፖሊስ በጎፋ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ አደረገ - ኢዜአ አማርኛ
ፌደራል ፖሊስ በጎፋ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 23/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በጎፋ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ አደረገ።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል፤ ለተጎጂዎች የተላከውን ድጋፍ አስረክበዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ አደጋው ከደረሰበት እለት ጀምሮ የፌዴራል ፖሊስ አባላት በስፍራው በመገኘት ሙያዊ እገዛ እያደረጉ መሆኑን ገልጸዋል።
በዛሬው እለት ደግሞ በተቋሙ የ4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ግምት ያላቸው የተለያዩ ቁሳቁሶችና ምግብ ነክ ድጋፎች መደረጋቸውን ገልጸዋል።
በቀጣይም የፖሊስ ህዝባዊ አገልግሎት እንዳለ ሆኖ የተጎዱ ወገኖችን በገንዘብም ይሁን በአይነት ድጋፉ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በአደጋው ምክንያት ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖችም ኮሚሽነር ጀነራሉ ሀዘናቸውን ገልጸዋል።