የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ - ኢዜአ አማርኛ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 22/2016(ኢዜአ)፦ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለመጪው ረቡዕ ሐምሌ 24 ቀን 2016 ዓ.ም አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቷል፡፡
በኢፌዴሪ ሕገ-መንግሥት አንቀፅ 58 (4) እና በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአሰራርና የአባላት ሥነ-ምግባር ደንብ ቁጥር 6/2008 አንቀፅ 15 (1 ና 2) መሰረት ምክር ቤቱ በዕረፍት ላይ እያለ የምክር ቤቱን ውሳኔ የሚሹ አስቸኳይ ጉዳዮች ሲያጋጥሙ የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ አስቸኳይ ስብሰባ ሊጠራ እንደሚችል ተደንግጓል፡፡
በዚህ መሰረትም ለረቡዕ ሐምሌ 24 ቀን 2016 ዓ.ም የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ አስቸኳይ ስብሰባ መጥራቱን ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
ስለሆነም የ6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በዕለቱ ከቀኑ 7 ከ 30 ጀምሮ ሪፖርት በማድረግ በአስቸኳይ ስብሰባው እንዲገኙ ምክር ቤቱ ጥሪ አቅርቧል፡፡