ቀጥታ፡

አየር መንገዱ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 7 ነጥብ 02 ቢሊየን ዶላር ገቢ አገኘ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 22/2016(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት  7 ነጥብ 02 ቢሊየን ዶላር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ።   

አየር መንገዱ የ2016 ዓ. ም ዓመታዊ  አፈጻጸም ላይ ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥቷል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው በሰጡት ማብራሪያ፤ አየር መንገዱ በበጀት ዓመቱ ስኬታማ ተግባራት ማከናወኑን  ገልፀዋል።

በተጠናቀቀው የ2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ 7 ነጥብ 02 ቢሊየን ዶላር ገቢ ማግኘቱን ገልፀው፤ ከአምናው ጋር ሲነጻጸር የ14 በመቶ ብልጫ እንዳለው ጠቁመዋል።

በጀት ዓመቱ 17 ነጥብ 1 ሚሊዮን መንገደኞችን ማጓጓዙን ገልጸዋል።

ከአጠቃላይ የግሩፑ አመታዊ ገቢ 5 ቢሊዮን ዶላር የተገኘው መንገደኞች በማጓጓዝ መሆኑን አብራርተዋል።

በበጀት ዓመቱ አምስት ዓለም አቀፍ የመንገደኛ መዳረሻ በመጨመር የዓለም አቀፍ በረራ መዳረሻዎችን ማሳደጉን ተናግረዋል። 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም