ቀጥታ፡

ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በጋምቤላ ክልል  ነገ አጀንዳ የማሰባሰብ ምክክር ይጀምራል

ጋምቤላ ፤ ሐምሌ 21/2016 (ኢዜአ) ፡- የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በጋምቤላ ክልል ከነገ ጀምሮ የአጀንዳ የማሰባሰብ  የምክክር መድረክ  እንደሚጀምር አስታወቀ።

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር መላኩ ወልደማሪያም ዛሬ ለጋዜጠኞች እንደገለጹት ኮሚሽኑ ካሁን በፊት በክልሉ በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ለአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት የሚሳተፋ ተወካዮችን አስመርጦ አዘጋጅቷል። 

በዚህ መሰረት ከነገ ሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለሰባት ተከታተይ ቀናት በክልሉ የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ እንደሚካሄድ ገልጸዋል።

በአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ ላይ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች የሚወክሉ ተሳታፊዎችን ጨምሮ በክልሉ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ የሲቪክ ማህበራት፣ የመንግስት አካላትና ተጽኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ይገኛሉ ብለዋል።

በአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ ከአንድ ሺህ 300 በላይ ተወካዮች እንደሚገኙም አመላክተዋል።

መድረኩ የክልሉ ባለድርሻ አካላት ሀገራዊ መግባባት ሊደረግባቸው ያስፈልጋል የሚሏቸውን እጅግ መሰረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች በህዝባዊ ውይይት የሚሰበስቡበት ወሳኝ ምዕራፍ ነው  ብለዋል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም