የኮይሻ ጊቤ 4 የኃይል ማመንጫ ግድብ ከታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ቀጥሎ ትልቁ ነው -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) - ኢዜአ አማርኛ
የኮይሻ ጊቤ 4 የኃይል ማመንጫ ግድብ ከታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ቀጥሎ ትልቁ ነው -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 20/2016(ኢዜአ)፦ የኮይሻ ጊቤ 4 የኃይል ማመንጫ ግድብ ከታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ቀጥሎ ትልቁ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።
በሺህዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች በፕሮጀክቱ በቀን እና በሌሊት በፈረቃ በመትጋት ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ዛሬ ለአስራ አራተኛ ጊዜ በፕሮጀክት ስፍራው ተገኝተው የሥራው ሂደት መገምገማቸውንም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።
ከስድስት ወራት በፊት ከነበረው ግምገማችን በኋላም ትርጉም ያለው እድገት መታየቱንም ተመልክተናል ብለዋል።