ኢትዮጵያ የጠቅላይ ሚኒስትሩን የአረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭ ለዓለም ታስተዋውቃለች- የወጣቶች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ፉአድ ገና - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ የጠቅላይ ሚኒስትሩን የአረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭ ለዓለም ታስተዋውቃለች- የወጣቶች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ፉአድ ገና
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 20/2016(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ኢኒሼቲቭ የሆነውን የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር ለአለም ታስተዋውቃለች ሲሉ የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ፉአድ ገና ገለጹ።
የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ፉአድ ገና ከኡሊያኖስክ ግዛት ምክትል አስተዳዳሪ አንድሪቭ ቫዲም ጋር በመሆን በኡሊያኖስክ የወዳጅነት ፓርክ የችግኝ ተከላ መረሀ ግብር አካሂደዋል፡፡
በብሪክስ የወጣቶች ጉባኤ ተሳታፊ የሆነው የኢትዮጵያ የልዑክ ቡድንና የኡሊያኖስክ ስቴት ፔዳጎጂካል ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንትም አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ፉአድ ገና ኢትዮጵያ እያካሄደች ስላለችው የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ ለችግኝ ተከላ መረሀ ግብሩ ተሳታፊዎች ገለጻ ማድረጋቸውን ከኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።