ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በጎፋ ዞን የመሬት መንሸራተት አደጋ የተጎዱ ቤተሰቦችን በስፍራው በመገኘት አጽናኑ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 20/2016(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በጎፋ ዞን የመሬት መንሸራተት አደጋ የተጎዱ ቤተሰቦችና የማኅበረሰብ አካላትን በስፍራው በመገኘት አጽናኑ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እስካሁን የ231 ዜጎችን ሕይወት እንደቀጠፈ በተረጋገጠው የጎፋ ዞን የመሬት መንሸራተት አደጋ የተጎዱ ቤተሰቦችና ማኅበረሰብ በአካል ለማፅናናት በስፍራው መገኘታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።


 

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ቀዳማዊት እመቤት ከቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ፣ ከቀድሞ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አባዱላ ገመዳ እንዲሁም ከሌሎች ከፍተኛ የፌደራል መንግሥት አመራሮች ጋር በስፍራው ሲገኙ በክልል ሃላፊዎች እና በማህበረሰቡ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም