ቀጥታ፡

ህንድ የኢትዮጵያ ወጣቶችን በስራ እድል ፈጠራ ዘርፍ እንደምትደግፍ ገለጸች

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 19/2016(ኢዜአ)፦ ህንድ የኢትዮጵያ ወጣቶችን በስራ እድል ፈጠራ ዘርፍ እንደምትደግፍ የህንድ የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር ሺሪማቲ ራክሻ ገለጹ።

የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ፉአድ ገና ከህንድ የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር ሺሪማቲ ራክሻ ጋር ተወያይተዋል።

በምክክራቸውም ሁለቱ ሀገራት በስራ ፈጠራ፤ በስታርታፕ፤ በባህል፤ በወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎትና በወጣት ለወጣት ግንኙነት ዙሪያ በትብብር ለመስራት ተስማምተዋል።

በቅርቡ በህንድ አዘጋጅነት በብሪክስ ማዕቀፍ ስር በሚዘጋጀው አመታዊ የወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያውያን ወጣት ስራ ፈጣሪዎች የሚሳተፉበትን መደላደል ለማመቻቸት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሂዶ ከስምምነት መደረሱን ከኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም