ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ፉአድ ገና ከኢራን የወጣቶች ሚኒስትር ዴኤታ ሲና ካልሆር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 19/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ፉአድ ገና ከኢራን የወጣቶች ሚኒስትር ዴኤታ ሲና ካልሆር ጋር ተወያይተዋል።

በኢትዮጵያና በኢራን ወጣቶች መካከል ድልድይ የሚሆን መደላደል ማመቻቸት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውም ተገልጿል።

በውይይታቸውም በአይሲቲ፣ በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ላይ በትብብር ለመስራት ተስማምተዋል።

የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ፉአድ ገና ከብሪክስ የወጣቶች ጉባኤ ጎን ለጎን ከብሪክስ አባል ሀገራት የወጣት ሚኒስትሮች ጋር የሁለትዮሽ ውይይት እያደረጉ እንደሚገኙ ከኢትዮጵያ ወጣቶች ካውንስል የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም