ዶክተር አለሙ ስሜ በትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ባሉት የኢንቨስትመንት እድሎች ዙሪያ ከተለያዩ ሀገራት ባለሃብቶች ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ዶክተር አለሙ ስሜ በትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ባሉት የኢንቨስትመንት እድሎች ዙሪያ ከተለያዩ ሀገራት ባለሃብቶች ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 19/2016(ኢዜአ)፦ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዶክተር አለሙ ስሜ በትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ባሉ የኢንቨስትመንት ዕድሎች ዙሪያ ከተለያዩ ሀገራት ከተውጣጡ የዓለም አቀፍ የንግድና ፋይናንስ ተቋም ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱም ዶክተር አለሙ ስሜ በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፍ 27 የሚሆኑ የኢንቨስትመንት መስኮች ተለይተው የአዋጭነት ጥናት እና ወጪ ግምት ስራ መሰራቱን አስረድተዋል፡፡
ሚኒስትሩ አክለውም በዘርፉ ካሉት የኢንቨስትመንት መስኮች ውስጥ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ እና የኃይል መሙያ ማሽን ቅድሚያ የሚሰጠው እና የመንግስት ተቀዳሚ የትኩረት መስክ መሆኑን ገልጸዋል።
በውይይቱ ላይ በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ እና የኃይል መሙያ ማዕከል፣ በሎጂስቲክስ፣ በባቡር እና መንገድ መሰረተ ልማት እንዲሁም ተጨማሪ የደረቅ ወደብ ግንባታ የኢንቨስትመንት እድሎች ዙሪያ ለባለሃብቶቹ ገለፃ ተደርጓል፡፡
የባለሀብቶቹ ቡድን በኢትዮጵያ ባለው ምቹና አዋጭ የቢዝነስ ከባቢ መሳባቸውን እና በትራንስፖርትና ሊጂስቲክስ ዘርፍ ላይ መዋዕለ ነዋያቸውን ለማፍሰስ ፍላጎት እንዳለቸው መግለጻቸውን ከሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል።