ቀጥታ፡

በፓሪስ ኦሎምፒክ ተሳታፊ ለሆነው የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ቡድን ልዩ አቀባበል ተደረገለት 

አዲስ አበባ ሐምሌ 18/2016(ኢዜአ)፡- በነገው ዕለት በይፋ በሚጀመረው 33ኛው የፓሪስ ኦሎምፒክና ፓራሊምፒክ ውድድር ላይ ኢትዮጵያን በመወከል የሚሳተፈው የመጀመርያ ዙር የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ቡድን ፈረንሳይ ደርሷል። 

ቡድኑ በፈረንሳይ ቻርልስ ደጎል (CDG) ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ ፓሪስ የሚገኘው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሚሲዮን እና በፈረንሳይ የሚኖሩ የዳያስፖራ አባላት ልዩ አቀባበል ተደርጎለታል። 


 

በተለያየ የእድሜ ክልል የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ−ኢትዮጵያውያን በስፍራው ተገኝተው ለኦሎምፒክ ቡድኑ ደማቅ አቀባበል ያደረጉ ሲሆን፣ ዝግጅቱ አገራችንን ለማስተዋወቅ መልካም አጋጣሚ የሚፈጥር መሆኑ መገለጹን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም