የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ለ2017 በጀት ዓመት የቀረበለትን 33 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ረቂቅ በጀት አፀደቀ - ኢዜአ አማርኛ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ለ2017 በጀት ዓመት የቀረበለትን 33 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ረቂቅ በጀት አፀደቀ
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 18/2016(ኢዜአ)፦ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ለ2017 በጀት ዓመት የቀረበለትን 33 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ረቂቅ በጀት አፀደቀ።
ከትናንት ጀምሮ መደበኛ ጉባዔውን እያካሄደ የሚገኘው የክልሉ ምክር ቤት በዛሬው ውሎው በክልሉ መንግስት የቀረበለትን የ2017 ረቂቅ በጀት ተወያይቶ በሙሉ ድምጽ አፅድቋል።
በዚህም ከተለያዩ ምንጮች የተገኘ በድምሩ 33 ቢሊየን 652 ሺህ 116 ብር አፅድቋል።
ይህም ከባለፈው የ2016 በጀት ጋር ሲነፃፀር የ8 ቢሊዮን ብር ወይም 32 በመቶ ብልጫ እንዳለው ተጠቅሷል።
ከበጀቱ መካከል 13 ቢሊየን ብር ከፌደራል መንግስት እንዲሁም ቀሪው 20 ቢሊዮን ብር በክልሉ የውስጥ ገቢ የሚሸፈን መሆኑ ተገልጿል።