የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት ናዳ ሳቢያ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የ5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት ናዳ ሳቢያ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የ5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 18/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት ናዳ ሳቢያ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የ5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡
የባንኩ የሥራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች በግላቸው እያደረጉ ካለው ድጋፍ በተጨማሪ የተደረገ ድጋፍ መሆኑን ከባንኩ የማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተለያዩ አካባቢዎች በተፈጥሮም ሆነ በሰው ሠራሽ አደጋዎች ለተጎዱ ወገኖች ፈጥኖ በመድረስ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ የሚገኝ ባንክ መሆኑም በመረጃው ተመላክቷል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በጤናው߹ በትምህርት߹ በአካባቢ ጥበቃ፣ በአረንጓዴ ልማት፣ በሰብአዊ ሥራ ድጋፍ እና በሌሎችም ዘርፎች ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ባለፉት አምስት ዓመታት ከ3 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉንም ባንኩ አስታውቋል፡፡