ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሥራ ኃላፊዎች ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 17/2016(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሥራ ኃላፊዎች ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖቻችን የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ፡፡

የባንኩ የሥራ ኃላፊዎች የገንዘብ ድጋፍ ያደረጉት በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት ናዳ ሳቢያ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ነው፡፡

ሁሉም የባንኩ ማህበረሰብ የበኩሉን ድጋፍ እንዲያደርግም ባንኩ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ባንኩ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባጋራው መረጃ መሰረት በሲቢኢ ብር ድጋፍ ለማድረግም ፦

👉የሲቢኢ ብር መተግበሪያዎን ከፍተው ‘ክፈል’ ‘Pay’ የሚለውን የአገልግሎት አማራጭ ይምረጡ፣

👉‘የዕርዳታ ማሰባሰብ’ ‘Fundraising’ ወደሚለው አማራጭ ይግቡ፣

👉‘Gofa Zone Land Slide Victims’ የሚለውን በመጫን የገንዘብ መጠን አስገብተው ልገሳ በቀላሉ ማድረግ እንደሚችሉ አስታውቋል።

በተጨማሪም ለዚሁ ዓላማ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተው የባንክ ሂሳብ ቁጥር

1000641522426 (BE GOFA ZONE BEMERET NADA LETEGODU) ድጋፍ ማድረግ እንደሚቻልም ባንኩ ገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም