"የትርክት ዕዳና በረከት" የተሰኘው የሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት መፅሃፍ ተመረቀ - ኢዜአ አማርኛ
"የትርክት ዕዳና በረከት" የተሰኘው የሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት መፅሃፍ ተመረቀ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 16/2016(ኢዜአ)፦ "የትርክት ዕዳና በረከት" የተሰኘው የሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት መፅሃፍ ተመርቋል።
በጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳይ አማካሪ ሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የተፃፈው "የትርክት ዕዳና በረከት" መፅሐፍ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ተመርቋል፡፡
በሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የተጻፈው "የትርክት ዕዳና በረከት" መጽሐፍ ምረቃ ላይ ከታደሙ ግለሰቦች ለተነሱ ጥያቄዎች ደራሲው ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በማብራሪያቸውም በውጭ ሀገራት ያሉ ኢትዮጵያውያን ልጆቻቸውን የኢትዮጵያን እውቀት እንዲማሩ ቢያደርጉ አሁን የምንጨቃጨቅበትን ጉዳዮች በንግግር መፍታት የሚያስችል እውቀት እንዳለን ይረዳሉ ብለዋል።
ዛሬ እውነቱን ስንናገር ሰው ባይሰማንም የነገው ትውልድ ግን ይሰማናል ያሉት የመፀሐፉ ደራሲ ገበያው የሚፈልገውን ሳይሆን እውቀትን የምናወርስበት ጉዳይ ላይ ማተኮር አለበን ነው ያሉት።
በተለይም ምሁራን እውቀታቸውን በሃላፊነት እንዲያካፍሉም ምክረ ሀሳባቸውን ሰጥተዋል።
ከበፊት ጀምሮ የኛ መሰረታዊ ችግር አለመነጋገር ነው ያሉት ሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በጠረጴዛ ዙሪያ ከተነጋገርን ብዙ ነገሮቻችን ቀላል መሆናቸውንም አስረድተዋል።
"የትርክት ዕዳና በረከት" መፅሐፍ በ46 ምዕራፎች የተከፋፈለ ሲሆን፤ 575 ገፆች ያሉት ነው፡፡