ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጎርጎራ ሪዞርትን በኢትዮጵያ ስካላይት ሆቴል ስር የማስተዳደር ኃላፊነትን ተረከበ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 16/2016 (ኢዜአ):- የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጎርጎራ ሪዞርትን በኢትዮጵያ ስካላይት ሆቴል ስር የማስተዳደር ኃላፊነትን ተረከበ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጎርጎራ ሪዞርትን በኢትዮጵያ ስካላይት ሆቴል ስር የማስተዳደር ኃላፊነትን ዛሬ በኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል በተደረገ የስምምነት ስነስርዐት መረከቡን አስታውቋል።


 

በስነ ስርዐቱ ላይ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ አረጋ ከበደ፣ ከፍተኛ የክልሉ የስራ ኃላፊዎች፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የንግድ ሥራ ዋና ኃላፊ አቶ ለማ ያዴቻ እና ሌሎች የኢትዮጵያ አየር መንገድ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በገበታ ለሀገር ፕሮጀክት የተገነቡትን ሀላላ ኬላ ሪዞርት፣ የወንጪ ኢኮ ሎጅ እንዲሁም የጨበራ ጩርጩራ የዝሆን ዳና ሎጅን የማስተዳደር ኃላፊነትን በቅርቡ ወስዶ ወደ ስራ በመግባት ለኢትዮጵያ ቱሪዝም ኢንደስትሪ ዕድገት የራሱን ድርሻ ለመወጣት ያላሰለሰ ጥረት እያደረገ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም