ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት በመሬት መንሸራተት አደጋ በተጎዱ ዜጎች የተሰማዉን ጥልቅ ኀዘን ይገልጻል

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ ከሰሞኑ ባጋጠመው የመሬት መንሸራተት አደጋ የኢፌዴሪ መንግሥት የተሰማዉን ጥልቅ ኀዘን ይገልጻል፡፡ ይህ መግለጫ እስከወጣበት ጊዜ ድረስ 157 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፤ ከፍተኛ የንብረት ውድመትም ደርሷል።

የፌዴራሉ መንግሥት በአጋጠመዉ አደጋ በጥልቅ ከማዘኑም ባሻገር የአደጋዉን ተጎጂዎች ለመታደግ፣ በናዳ ውስጥ የተቀበሩ ሰዎችን ለማፈላለግና የነብስ አድን ሥራዎችን ለማከናወን እንዲሁም ጉዳት የደረሰባቸዉን ዜጎች መልሶ ለማቋቋምና የደረሰውን የጉዳት መጠን ለመለየት ከተለያዩ አካላት የተውጣጡ አስቸኳይ የአደጋ መከላከል ግብረ ኃይል አቋቁሞ ወደ ስፍራው ልኳል፡፡ የአደጋዉን የጉዳት መጠንና የተጎጂዎች አጠቃላይ መረጃ በቀጣይ በተደራጀ አግባብ የሚገለጽ ይሆናል፡፡

መንግሥት ለተጎጂ ቤተሰቦች መጽናናትንና ብርታትን፣ የአካል ጉዳት ለደረሰባቸዉ በቶሎ ማገገምን ይመኛል። አስፈላጊዉን የመልሶ ማቋቋም ሥራን ከአካባቢው የመንግሥት መዋቅር ጋር አጠናክሮ ይቀጥላል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም