ቀጥታ፡

አቶ ተመስገን ጥሩነህ በጎፋ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ በዜጎች ላይ በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ16/2016(ኢዜአ)፦ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ ድንገተኛ የመሬት ናዳ አደጋ በደረሰው አስከፊ ጉዳት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገለጹ።

አቶ ተመስገን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት ናዳ በዜጎቻችን ላይ በደረሰው አደጋ የተሰማኝን ጥልቅ ልባዊ ሀዘን ለመግለፅ እወዳለሁ ሲሉ ገልጸዋል።

በአደጋው ጉዳት ለደረሰባቸው የተጎጂ ቤተሰቦች እና ዘመድ ወዳጆች ሁሉ መፅናናትን እመኛለሁ።

በቀጣይም በአደጋው ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎቻችንን መልሶ ለማቋቋም የጉዳቱን ሰለባዎች ለመርዳት መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ ያደርጋል ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም