ቀጥታ፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከተመድ ምክትል ዋና ጸሐፊ አሚና መሀመድ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 16/2016(ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምክትል ዋና ጸሐፊ አሚና መሀመድ ጋር  ተወያይተዋል።

ውይይቱ የኢትዮጵያ የልማት እንቅስቃሴና የአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ መሆኑ ተመላክቷል።


 

በተጨማሪም መጪውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጉባኤ አስመልክቶ መምከራቸው ተገልጿል።

አምባሳደር ታዬ ምክትል ዋና ጸሐፊዋ በተመድ የልማት ስርዓት ውስጥ እያበረከቱት ስለሚገኘው የአመራርነት ሚና ምስጋና ማቅረባቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም