ቀጥታ፡

በሶማሌ ክልል ዶሎ ዞን  ዳራቶሌ ወረዳ 90 ሚሊዮን ብር በሚጠጋ ወጪ የተገነባ የፀሐይ ሐይል ማመንጫ ፕሮጀክት ተመረቀ

ዶሎ፤ ሐምሌ 13/2016(ኢዜአ)፦ በሶማሌ ክልል ዶሎ ዞን ዳራቶሌ ወረዳ 90 ሚሊዮን ብር በሚጠጋ ወጪ የተገነባ የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

ፕሮጀክቱን መርቀው ሥራ ያስጀመሩት የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ ኢንጂነር ሡልጣን ወሊ (ዶ/ር)  እና የሶማሌ ክልል ከፍተኛ አመራር አባላት ናቸው።

ፕሮጀክቱ 725 ኪሎ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም እንዳለው በምረቃው ሥነ ሥርዓት ላይ ተገልጿል።


 

ፕሮጀክቱ ከሰባት ሺህ በላይ ቤተሰቦችንና የትምህርት፣ የጤናና ሌሎች ማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማትን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተጠቁሟል።

የወረዳው የሀገር ሽማግሌዎችና ነዋሪዎች በፕሮጀክቱ ግንባታ የዘመናት የልማት ጥያቄያቸው በመመለሱ ደስተኛ መሆናቸውን ነው የገለጹት።

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ አመራር አባላት፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም