በቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር በመንግሥት እና በህዝብ ተሳትፎ የተገነቡ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተመረቁ - ኢዜአ አማርኛ
በቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር በመንግሥት እና በህዝብ ተሳትፎ የተገነቡ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተመረቁ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 13/2016(ኢዜአ)፦ በቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር በመንግሥት እና በህዝብ ተሳትፎ የተገነቡ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተመረቁ።
በመርኃ ግብሩ ላይ በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ፍቃዱ ተሰማ፣ የቢሾፍቱ ከተማ ከንቲባ አለማየሁ አሰፋ ፣ የአየር ኃይል ዋና አዣዥ ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ፣ የኦሮሚያ ክልል የሥራ ኃላፊዎችና የከተማዋ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
በከተማ አስተዳደሩ የተገነቡት መሰረተ ልማቶች፣ የመስሪያ ሼዶች፣ የገበያ ማዕከላት፣ የተለያዩ አገልግሎት የሚሰጡ ህንጻዎች፣ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችንና ሌሎችን ያጠቃለሉ ናቸው።
በአጠቃላይ የተለያዩ አገልግሎት የሚሰጡ 175 ፕሮጀክቶች ተገንብተው ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል።
በኦሮሚያ ክልል በመንግሥት እና በህዝብ ተሳትፎ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብተው ለአገልግሎት ክፍት እየተደረጉ ይገኛሉ።