ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ተወካይ ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ተወካይ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 12/2016(ኢዜአ)፦ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የስራ ጊዜያቸውን ካጠናቀቁት የተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ተወካይና የቀጠናው ዳይሬክተር ሆነው ካገለገሉት ኦሬሊያ ፓትሪዚያ ካላብሮ ጋር ተወያዩ።
የኢትዮጵያ መልካም ወዳጅ የነበሩት ኦሬሊያ ፓትሪዚያ ካላብሮ በድርጅቱ በነበራቸው የስራ ጊዜ ሀገራችን ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ልማትን በመደገፍ ላሳዩት አመራርነት እያመሰገንኩ በቀጣይም በከተማ አስተዳደሩ በሴቶች ክህሎት ማበልፀጊያና የስራ ዕድል ፈጠራ ዙሪያ የጀመርናቸውን ተግባራት በአጋርነት መስራትን ለማስቀጠል ከስምምነት ላይ ደርሰናል ሲሉ ከንቲባዋ ገልጸዋል፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በራሳቸውና በከተማ አስተዳደሩ ስም ቀጣይ የስራ ዘመናቸው የተቃና እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን መግለጻቸውን ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።