ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ለታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ላደረገው ድጋፍ ሽልማት ተበረከተለት

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 12/2016(ኢዜአ):- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ላደረገው ድጋፍ የወርቅ ደረጃ ሽልማት ተበረከተለት።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከምስረታው ጀምሮ ባካሄዳቸው የተለያዩ የሩጫ መርሃግብሮች ለሰጠው ያልተቋረጠ ድጋፍ እና ለሩጫ መርሐግብሮቹ ስኬታማነት ላበረከተው አስተዋፅኦ ‘የወርቅ ደረጃ’ የዕውቅና ሽልማት ተበርክቶለታል።

ለአየር መንገዱ የተዘጋጀውን ሽልማት አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ እና አትሌት ገዛኸኝ አበራ አበርክተዋል፡፡


 

በሽልማት አሰጣጥ ስነ-ስርዓቱ ላይ የቱሪዝም ሚኒስትር ናሲሴ ጫሊን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም