ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በጫካ ፕሮጀክት ሀገር በቀል የአረንጓዴ አሻራ ችግኞችን ተከሉ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በጫካ ፕሮጀክት ሀገር በቀል የአረንጓዴ አሻራ ችግኞችን ተከሉ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 12/2016(ኢዜአ)፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች ጋር በመሆን በጫካ ፕሮጀክት ሀገር በቀል የአረንጓዴ አሻራ ችግኞችን ተክለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት በዘንድሮው የአረንጓዴ ዓሻራ መርሃ ግብር ሁሉም ዜጋ ተካፋይ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል።
“የምትተክል ሀገር፣ የሚያፀና ትውልድ” በሚል መሪ ሃሳብ የዘንድሮ የ #አረንጓዴ ዓሻራ መርሃ ግብር እየተካሄደ ይገኛል።
የባህር ዛፍን በሀገር በቀል የዛፍ ዝርያዎች የመተካቱ ሂደት ተጠናክሮ መቀጠሉን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።