ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ሰብስብ አባፍራን በፕሬዝዳንትነት መረጠ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 11/2016(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 10ኛ ጠቅላላ መደበኛ ጉባኤ የምክር ቤቱን ፕሬዝዳንት ጨምሮ ምክትል ፕሬዝዳንትና ስራ አመራር ቦርድ አባላትን መርጧል።

ላለፋት ስድስት ዓመታት ምክር ቤቱን በፕሬዝዳንትነት ሲያገለግሉ የነበሩት ኢንጅነር መላኩ እዘዘውን በምርጫ የተኩት የኦሮሚያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የነበሩት ሰብሰብ አባፍራ ናቸው።

ምክር ቤቱ አይናለም አባይነህን(ዶ/ር) ምክትል ፕሬዝዳንት በማድረግ የመረጠ ሲሆን፤ የሥራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትም በአዲስ ተተክተዋል።

ላለፉት ዓመታት በስራ ላይ የነበረው አመራር በተለያዩ ምክንያቶች ጠቅላላ ጉባኤ አላካሄደም።

ይሁንና የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በሰጠው አቅጣጫ ጉባኤውን ዛሬ አካሂዷል።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ከተቋቋመ 77 ዓመታትን አስቆጥሯል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም