የ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ - ኢዜአ አማርኛ
የ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 11/2016(ኢዜአ)፦ የ2016 ትምህርት ዘመን በወረቀትና በበይነ መረብ ሲሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ፡፡
በተመሳሳይ መልኩ በትግራይ ክልል እየተሰጠ ያለው ፈተና ነገ አርብ ከሰዓት በፊት እንደሚጠናቀቅ አገልግሎቱ አስታውቋል፡፡
ባለድርሻ አካላት ፈተናው በስኬት እንዲጠናቀቅ ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አገልግሎቱ ማመስገኑን ከአገልግሎቱ ማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡