የአየርላንዱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሚሼል ማርቲን አዲስ አበባ ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
የአየርላንዱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሚሼል ማርቲን አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 10 /2016 (ኢዜአ)፡- በአየርላንዱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሚሼል ማርቲን የተመራ ልዑክ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባ ገብቷል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በአዲስ አበባ በሚኖራቸው ቆይታም ከኢትዮጵያ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሚሼል ማርቲን ከያዙት ኃላፊነት በተጨማሪ የአገሪቱ መከላከያ ሚኒስትርም ናቸው።