ኢትዮጵያ ከግሪክ ጋር ያላትን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ትሰራለች -አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ ከግሪክ ጋር ያላትን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ትሰራለች -አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 10/2016(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ ከግሪክ ጋር ያላትን ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር በትኩረት ትሰራለች ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ገለጹ።
አምባሳደር ምስጋኑ በግሪክ የኢትዮጵያ የክብር ቆንስል ጽህፈት ቤትን መርቀው ከፍተዋል።
በመክፈቻ ስነ-ስርዓቱ ላይ የግሪክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎች፣ በግሪክ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ተወካዮች፣ የቢዝነስ ማህበረሰብ አባላት እንዲሁም ታዋቂ ግለሰቦች ተገኝተዋል።
በወቅቱም አምባሳደር ምስጋኑ በግሪክ የኢትዮጵያ የክብር ቆንስል ሆነው ለተሾሙት ጂዮርጂዮስ ቢካስ የሹመት ደብዳቤያቸውን ማስረከባቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
የክብር ቆንስል ጽህፈት ቤቱ በይፋ ወደ ስራ መግባቱን አስመልክቶም አምባሳደር ምስጋኑ እንደገለጹት ጂዮርጂዮስ ቢካስ በግሪክና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር በትኩረት ይሰራሉ።
በተለይም በንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፎች ያለውን ግንኙነት ለማሳደግ ከፍ ያለ አስተዋፅኦ እንደሚያደርጉም ያላቸውን እምነት ገልፀዋል።