በታች አርማጭሆ ወረዳ 7 ሺህ 500 ጥይት ተያዘ - ኢዜአ አማርኛ
በታች አርማጭሆ ወረዳ 7 ሺህ 500 ጥይት ተያዘ
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 10/2016(ኢዜአ)፦በታች አርማጭሆ ወረዳ ከሳንጃ ወደ ሰጋሎ በባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪ በድብቅ ሲጓጓዝ የነበረ ሰባት ሺህ አምስት መቶ የክላሽ ጥይት መያዙን የሰሜን ምዕራብ ዕዝ አንድ ክፍለ ጦር ገለጸ።
የክፍለ ጦሩ አዛዥ ኮሎኔል ግርማ መሃመድ እንደገለጹት አርማጭሆ ወረዳ ከሳንጃ ወደ ሰጋሎ በባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪ ባጃጅ በድብቅ ሲጓጓዝ የነበረ ሰባት ሺህ አምስት መቶ የክላሽ ጥይት ፈንዲቃ ላይ ተይዟል።
የህገ-ወጥ ድርጊቱ ተሳታፊዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገ ነው ያሉት አዛዡ ሠላም ፈላጊው ህብረተሰብ መረጃ በመስጠት እያደረገ ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።
በወረዳው የመንግስትን የሠላም አማራጭ የተቀበሉ 9 የፅንፈኛው ኃይል ታጣቂዎች ከነሙሉ ትጥቃቸው እጅ መስጠታቸውንም አዛዡ ተናግረዋል።
ሠላም ብቸኛው አማራጭ መሆኑን የተረዱ የፅንፈኛውና የዘራፊው ቡድን ታጣቂዎች ከግጭት የምናተርፈው ነገር የለም፤ጥያቄዎችን በሠላማዊ መንገድ መፈታት እየተቻለ ነፍጥ አንግቦ ጫካ መግባት ውጤት አያመጣም በማለት እጃቸውን ለመስጠት የወሰኑ መሆናቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።