የኢትዮጵያ ደን ልማት እና የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ አመራርና ሠራተኞች በወላይታ ዞን ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ችግኝ ተከሉ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ደን ልማት እና የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ አመራርና ሠራተኞች በወላይታ ዞን ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ችግኝ ተከሉ
ሀዋሳ ፤ሐምሌ 10/2016 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ደን ልማት እና የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ አመራሮችና ሠራተኞች በወላይታ ዞን ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ የቀርከሃ ችግኝ ተከላ እያከናወኑ ነው።
የኢትዮጵያ ደን ልማትና የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በመተባበር በወላይታ ዞን ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ የተቀናጀ ቀርከሃ ልማት ሥራ እያከናወኑ መሆናቸው ተገልጿል።
ተቋማቱ በወላይታ ዞን ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ላይ የተቀናጀ የቆላ ቀርከሃ ልማት እያከናወኑ ያሉት በ33 ነጥብ 19 ሄክታር መሬት ላይ ነው።
በዛሬው በአረንጓዴ አሻራ ልማት መርሀግብር የተተከሉ የቀርከሃ ችግኞችም ይህን ልማት ለማጠናከር በማሰብ መሆኑን ተገልጿል።
በቀርከሃ ችግኝ ተከላው ላይ የሁለቱ ተቋማት አመራሮች፣ ሠራተኞችና የወላይታ ዞን አስተዳደር አካላት በመሳተፍ ላይ ናቸው።
የተቀናጀ የቀርከሃ ልማት ሥራው በአካባቢው የተራቆቱ መሬቶችን እንዲያገግሙ እና የአካባቢው ማህበረሰብ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆን ጉልህ ሚና እንዳለው ተመላክቷል።