ቀጥታ፡

ዲጂታል ዲፕሎማሲ እና ሰው ሰራሽ አስተውሎት(AI) ለዲፕሎማሲ ባለው አበርክቶ ዙሪያ ለአዲስ ተሿሚ አምባሳደሮች ሥልጠና ተሰጠ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 9/2016(ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለአዲስ ተሿሚ አምባሳደሮች በወቅታዊ ሀገራዊ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ እየሰጠ ያለው የቅድመ ሥምሪት ስልጠና ዛሬም ለአምስተኛ ቀን ቀጥሏል።

በዛሬው ዕለትም ዲጂታል ዲፕሎማሲ እና ሰው ሰራሽ አስተውሎት(AI) ለዲፕሎማሲ ባለው አበርክቶ ዙሪያ ለአዲስ ተሿሚ አምባሳደሮች ሥልጠና ተሰጥቷል።


 

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና(ዶ/ር) እና የኢንፎርሜሽን መረብ ደኀንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ትዕግስት ሀሚድ ሥልጠናውን ሰጥተዋል።

ሥልጠናውን በአወያይነት እየመሩ ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ መሆናቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም