በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ መልቀቂያ ፈተና እየተሰጠ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ መልቀቂያ ፈተና እየተሰጠ ነው
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 9/2016(ኢዜአ)፦ የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ መልቀቂያ ፈተና ከሚሰጥባቸው ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መካከል አንዱ በሆነው የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ፈተናው እየተሰጠ ይገኛል።
የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በዩኒቨርሲቲው ተገኝተው የፈተና አሰጣጡን እየተመለከቱ ነው።
ፈተናው በኮምፒውተር እና በወረቀት እየተሰጠ ይገኛል።
የማኅበራዊ ሣይንስ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ባለፈው ሣምንት መሰጠቱ ይታወቃል፡፡