በሽግግር ፍትህ፣ በሀገራዊ ምክክር እና የአደጋ ስጋት አመራር ላይ ለአዲስ ተሿሚ አምባሳደሮች ገለፃ ተደረገ - ኢዜአ አማርኛ
በሽግግር ፍትህ፣ በሀገራዊ ምክክር እና የአደጋ ስጋት አመራር ላይ ለአዲስ ተሿሚ አምባሳደሮች ገለፃ ተደረገ
አዲስ አበባ፣ሐምሌ 8/2016 (ኢዜአ):- አራተኛ ቀኑን በያዘው የአዲስ ተመዳቢ አምባሳደሮች ስልጠና በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ በሀገራዊ ምክክር እና በአደጋ ስጋት አመራር ፖሊሲ ላይ ገለፃ መደረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ የውይይት መድረኩን መምራታቸውም ተመላክቷል።
የኢትዮጵያ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ፣ የሀገራዊ ምክክር እና የአደጋ ስጋት አመራር ፖሊሲን ጨምሮ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ገለፃ ቀርቧል።
አምባሳደሮቹ የእነዚህን ፖሊሲዎች ትግበራ ማፋጠን እና በቀጣይ ፈተናዎችን ለመቅረፍ ባለድርሻ አካላትን ማሳተፍ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ሰፊ ማብራሪያ መሰጠቱ ተገልጿል።