ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኮቪድ -19ኝ ለመከላከልና ለመግታት በአለም አቀፍ ደረጃ ላበረከተው የላቀ አስተዋፅዖ ዕውቅና ተሰጠው

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 8/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮቪድ-19ኝ ለመከላከል እና ለመግታት በተደረገው ዓለም አቀፍ ርብርብ ላበረከተው የላቀ አስተዋፅዖ በቶሮንቶ ካናዳ በተካሄደ የመጀመሪያው ድህረ ኮቪድ ኮንፈረንስ የዕውቅና ሽልማት ተበረከተለት።

ሽልማቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት በአፍሪካ እና በተለያዩ ክፍለ ዓለማት የሚገኙ አገራት ወረርሽኙን ለመከላከል ጥቅም ላይ ያዋሏቸውን የተለያዩ የህክምና ቁሳቁሶች በተቀልጣፋ አገልግሎቱ በማጓጓዝ የበርካቶችን ህይወት ለመታደግ በተደረገው ጥረት ለነበረው የጎላ ሚና የተሰጠ ነው።

ኮንፈረንሱ የተዘጋጀው በDevelopment International Initiatives (LDII) ፣በምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ድርጅት(ኢጋድ) እና የተለያዩ ወረርሽኞችን በጋራ መከላከል ላይ አተኩረው በሚሰሩ የስራ አጋሮች ትብብር መሆኑን የአየር መንገዱ መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኮቪድ -19ኝ ለመከላከልና ለመግታት በአለም አቀፍ ደረጃ ላበረከተው የላቀ አስተዋፅዖ ዕውቅና ተሰጠው

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም