ሮድሪ የአውሮፓ ዋንጫ ኮከብ ተጫዋች ሆኖ ተመረጠ - ኢዜአ አማርኛ
ሮድሪ የአውሮፓ ዋንጫ ኮከብ ተጫዋች ሆኖ ተመረጠ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 7/2016 (ኢዜአ)፦ የ28 ዓመቱ ስፔናዊ የተከላካይ አማካይ ሮድሪ የ17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ ኮከብ ተጫዋች ሆኖ ተመርጧል።
በጀርመን አስተናጋጅነት ከሰኔ 7 ቀን 2016 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ውድድር ዛሬ ማምሻውን ተጠናቋል።
ስፔን እንግሊዝን 2 ለ 1 በማሸነፍ የአውሮፓ ዋንጫ ባለቤት ሆናለች።
የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ለ28 ዓመቱ የማንችስተር ሲቲ የተከላካይ አማካይ ሮድሪ የውድድሩ ኮከብ ተጫዋች ሽልማት አበርክቷል።
እንግሊዛዊው ሀሪ ኬን፣ ስፔናዊው ዳኒ ኦልሞ፣ ኔዘርላንዳዊው ኮዲ ጋፕኮ፣ ጀርመናዊው ጀማል ሙሲያላ፣ ስሎቫኪያዊው ኢቫን ሽራንዝና የጆርጂያው ጆርጄስ ሚካውታድዛ በተመሳሳይ 3 ጎሎችን በማስቆጠር የኮከብ ግብ አግቢ ሽልማቱን በጋራ ወስደዋል።
የ17 ዓመቱ ታዳጊ ላሚን ያማል የአውሮፓ ዋንጫ ኮከብ ወጣት ተጫዋች ሆኖ ተመርጧል።
እንግሊዛዊው ጆርዳን ፒክፎርድና የውድድሩ ኮከብ ግብ ጠባቂ ሽልማትን ወስዷል።