ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ የልማት ፕሮጀክቶች ከሀገርም ባለፈ የጎረቤት አገራትን ተጠቃሚነት ታሳቢ ያደረጉ ናቸው- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር 

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 7/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የልማት ፕሮጀክቶች ከሀገርም ባለፈ የጎረቤት አገራትን ተጠቃሚነት ታሳቢ ያደረጉ መሆናቸውን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ፍሰሃ ሻውል ገለጹ።

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ፍሰሃ ሻውል፤ ኢትዮጵያ ከራሷም ባለፈ ለአህጉራዊ ልማትና የጋራ ተጠቃሚነት የላቀ ሚናዋን እየተወጣች መሆኑን ገልጸዋል።

ከጥንት እስካሁንም ቀጣናዊ ትሰስርን የማጠናከርና ከጎረቤት አገራት ጋር አብሮ የመልማት እቅድና ተግባራዊ እንቅስቃሴዋን አጠናክራ መቀጠሏን ነው የተናገሩት።

በተለይም በኃይል አቅርቦት፣ የባቡር መሰረተ ልማት፣ በቴሌኮምና የውሃ ልማት አቅርቦት ጎረቤት አገራትን ተጠቃሚ እያደረገች መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ የልማት ፕሮጀክቶች ከሀገርም ባለፈ የጎረቤት አገራትን ተጠቃሚነት ታሳቢ ያደረጉ ናቸው ብለዋል።

ከልማት ትሰስርም ባለፈ አህጉራዊ ሰላምና መረጋጋት ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት የመሪነት ሚናዋን አጠናክራ ቀጥላለች ሲሉ ተናግረዋል።

በቅርቡ የጎረቤት ሀገራት የድንበር አስተዳደር የጋራ ኮሚሽን ስብሰባዎች በተከታታይነት እንደሚካሄዱ አምባሳደር ፍሰሃ ገልጸዋል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም