የጨልጨል መስኖ ልማት ፕሮጀክት በ5 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ግንባታው በመካሄድ ላይ ይገኛል

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 4/2016(ኢዜአ)፦ የጨልጨል መስኖ ልማት ፕሮጀክት በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ባሌ ዞን ራይቱ እና ጊኒር ወረዳዎች መካከል በ5 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ግንባታው በመካሄድ ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡


 

የፕሮጀክቱ ግንባታ ሲጠናቀቅ 4 ሺህ 145 ሔክታር መሬት በመስኖ በማልማት ከዘጠኝ ሺህ በላይ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተገልጿል፡፡

ፕሮጀክቱ በታህሳስ 2012 ዓ/ም የተጀመረ ሲሆን በ2018 በጀት ዓመት መጨረሻ ለማጠናቀቅ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ከመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም