ለ #ጽዱኢትዮጵያ ንቅናቄ ጥሪ ስናቀርብ ዜጎቻችን በከፍተኛ ተነሳሽነት በሥራው ተሳትፈዋል -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) 

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 4/2016(ኢዜአ)፦ ለ #ጽዱኢትዮጵያ ንቅናቄ ጥሪ ስናቀርብ ዜጎቻችን በከፍተኛ ተነሳሽነት በሥራው ተሳትፈዋል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ። 

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ዋናው አላማችን አካባቢያችንን ሳቢ በማድረግ መፀዳጃ ቤት የመጠቀም ባህላችንን ከመሠረቱ ማዳበር ነበር ብለዋል።

ዛሬ በዜጎቻችን በዋጋ የማይተመን የልብ መዋጮ እና እምነት የተገነቡትን ሥራዎች በቦታው በመገኘት መገምገማቸውንም ገልጸዋል።

ከፍተኛ ጥራት ባላቸው ጠንካራ እና ዘመን ተሻጋሪ በሆኑ ቁሶች በመጠቀም ደረጃቸውን የጠበቁ የህዝብ መፀዳጃ ቤቶች ለመገንባት ቁርጠኝነት ይዘናል ሲሉም ገልጸዋል። 

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው ይህ የሥራው መጀመሪያ ነው። በእናንተ ያላሰለሰ ድጋፍ የጀመርናቸውን ሥራዎች እናስፋፋለን ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም