መማሬ ለስራዬ ዋስትና ሆኖኛል - የ54 አመቷ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ

ሰመራ ፤ሐምሌ 4/2016 (ኢዜአ)፦የ 54 አመቷ ወይዘሮ አዲስ ተስፋዬ በሰመራ ዩኒቨርሲቲ የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተፈታኝ መማሬ  ለስራዬ ዋስትና ሆኖኛል ይላሉ  ፡፡

ወይዘሮ አዲስ ተስፋዬ በአፋር ክልል በገቢ ረሱ ዞን አሚባራ ወረዳ አዋሽ አርባ ከተማ የነገው ተስፋ ትምህርት ቤት የ12 ክፍል ተማሪ ናቸው ።

መማራቸው   ለሚተዳደሩበት ስራ ዋስትና ሆኖኛል ፤ወደ ፊትም አቅሜ እሰከፈቀደ እማራለሁ ይላሉ። 

ብዙዎች በዚህ እድሜዬ በመማሬ ቢገርማቸውም መማሬ  ለስራ ቦታዬ የሚፈለግብኝን የትምህርት ማስረጃ በማቅረብ  ለስራ ዋስትና ሆኖኛልም በማለት ያክላሉ።

በአዋሽ አርባ ውጊያ ቴክኒክ ትምህርት ቤት በምግብ  አብሳይነት  የሚያገለግሉት   ወይዘሮ አዲስ በሰመራ ዩኒቨርሲቲ   ለፈተና በመጡበት ወቅት  የዩኒቨርሲቲው መልካም አቀባበልንም   አድንቀዋል ።

የሶስት ልጆች እናት የሆኑት ወይዘሮ አዲስ እድሌ ሰምሮልኝ ጥሩ ውጤት ካመጣሁ በዚሁ ዩኒቨርሲቲ ትምህርቴን መቀጠል እፈልጋለሁ  ሲሉ የቀጣይ እቅዳቸውን  ይገልጻሉ ።

“ሌሎችም  የእኔን ሁኔታ ተመልክተው መነሳሳት አለባቸው ፤ለትምህርት የሚረፍድ ጊዜ የለም” በማለት  ምክረ ሀሳባቸውን ሲለግሱ።

በገቢ ረሱ ዞን ትምህርት ቤቶች ጽህፈት ቤትም የወይዘሮዋን  አርያነት  “ለብዙዎች ሞዴል የሆኑ” እናት በማለት አሞካሽቷቸዋል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም