ሀገርን መስሪያ፣ ትውልድን መቅረጫ፣ ባህልና ወግን ማስተዋወቂያ ቀመሩ ሚዲያ ነው- አቶ ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 4/2016(ኢዜአ)፦ሀገርን መስሪያ፣ ትውልድን መቅረጫ፣ ባህል እና ወግን ማስተዋወቂያ ቀመሩ ሚዲያ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።


 

አቶ ተመስገን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው “ሚዲያ ለሀገር” በሚል መሪ ሐሳብ በተዘጋጀው መርኃ ግብር ላይ ዕውቅና የተቸራችሁ መገናኛ ብዙሃን እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ ሲሉ አስፍረዋል።


 

በሀገር ግንባታ፣ በትውልድ ቅብብሎሽ፣ ታሪክን በመሰነድ እና መረጃን በማቀበሉ ረገድ የሚዲያ ድርሻ ትልቅ ነው ብለዋል።

በመሆኑም ሚዲያዎች ለብሔራዊ ጥቅም፣ ለሀገር አንድነት እንዲሁም ማህበረሰባዊ ትስስርን የሚያጠናክሩ ስራዎች ላይ የበለጠ ትኩረት እንድትሰጡ አደራ እላለሁ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም