በምስራቅ ሐረርጌ ዞን የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በዞኑ ጎሮ ጉቱ ወረዳ ተጀምሯል - ኢዜአ አማርኛ
በምስራቅ ሐረርጌ ዞን የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በዞኑ ጎሮ ጉቱ ወረዳ ተጀምሯል
ሐረር ፤ ሐምሌ 03/2016 (ኢዜአ)፡- በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሐረርጌ ዞን የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በዞኑ ጎሮ ጉቱ ወረዳ ተጀምሯል።
በመርሐ ግብሩ የክልሉ፣ ዞንና የወረዳው የመንግስት ሥራ ኃላፊዎች፣ አርሶ አደሮች እና ሌሎች የማህበረሰቡ ክፍሎች ተገኝተዋል፡፡
"የምትተክል አገር የሚያፀና ትውልድ " በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ ያለው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በዞኑ ጎሮ ጉቱ በወረዳ ቡርቃ ጃለላ ተራራ ላይ የችግኝ ተከላ ተጀምሯል።
አርሶ አደሮች፣ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት የአረንጓዴ አሻራው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ በተከናወኑ የተፋሰስ ልማት ላይ እየተካሄደ ነው።
በዞኑ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከ324 ማሊዮን በላይ ችግኝ ለመትከል እቅድ መያዙን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ጌታሁን ንጋቱ ተናግረዋል።
ከሚተከሉ ችግኞች ውስጥም 40 በመቶ የሚሆኑት ለምግብነት የሚውሉ፤ እንዲሁም 60 በመቶ የደን እና ጥምር ደን እንዲሁም የእንስሳት መኖ መሆናቸውን ተናግረዋል።