ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የሚዲያ ለሀገር 2016 ልዩ ተሸላሚ ሆነ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 3/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት በተካሄደው የሚዲያ ለሀገር 2016 ልዩ ተሸላሚ ሆኗል።

በመርሃ ግብሩ ላይም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት መገናኛ ብዙኃን የኢትዮጵያን ልክ፣ እውነትና መሻት ለዓለም ሊያሳውቁ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ያገኘውን የእውቅና ሽልማትም ዋና ስራ አስፈጻሚው ሰይፈ ደርቤ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ተቀብለዋል።

መንግስት ያዘጋጀው ዓመታዊው የሚዲያ ለሀገር 2016 የእውቅና መርሐ ግብር የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች፣ የመገናኛ ብዙኃን ኃላፊዎችና ጋዜጠኞች በተገኙበት ተካሂዷል።

በመርሐ ግብሩም 11 የሕዝብና የንግድ መገናኛ ብዙኃን የተቀመጠውን ሀገራዊ ምዘና በማሟላት እውቅና ተሰጥቷቸዋል።

አንጋፋው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ብቸኛ የዜና አውታር በመሆን ሀገርና ህዝብን እያገለገለ በመሆኑ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዩ ሽልማት ተበርክቶለታል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በዚህ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት መገናኛ ብዙኃን የኢትዮጵያን ልክ፣ እውነትና መሻት ለዓለም ሊያሳውቁ እንደሚገባ ተናግረዋል።

የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም ማስከበር ኃላፊነታቸው መሆኑን በመገንዘብ ተግተው እንዲሰሩም ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም